የእሬቻ በዓል ይከበርበታል በተባለው ወንዝ ውስጥ የአንበሳ አውቶብስ ከጫናቸው ሙሉ ተሳፋሪዎች ጋር መውደቁ ታወቀ

በአዲስ አበባ አንበሳ የከተማ አውቶብስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ጀርባ ባለ ወንዝ መውደቁ ተሰማ።

አደጋው መስከረም 9፣2012 – 12:30 ግድም እንደደረሰ ሰምተናል። አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ ከየትኛው አቅጣጫ እንደመጣም ለጊዜው አልታወቀም ተብሏል።

እስካሁንም ምን ያህል ሰው ህይወት እንዳለፈ አልታወቀም ተብሏል።ይህንኑ አደጋ በተመለከተም 12 አምቡላንስ መመደቡን ሰምተናል።

የሰው ህይወትም ለማትረፍ ክሬን እና ሌሎች ከባ ድ ማሽነሪዎች ወደ ቦታው ተስዷል ተብሏል።አደጋው ያገኛቸው ተሳፋሪዎችም ወደ ዘውዲቱ እና አቤት ሆስፒታል ተወስደዋል።

ሸገር ወሬውን ከእሳት እና ድንገተኛ ኮምንኬሽን ሰምቷል።
አንበሳ አውቶብሱ ሙሉ ሰው እንዳጫነ ነው ተብሏል።ስንት ቁጥር አውቶብስ እንደሆነም ለጊዜው አልታወቀም መባሉን ሰምተናል።