የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ አዲሱ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ ።

“ይህንን ደንብ አንቀበለውም፣ ከፍርድ ቤት እገዳ ለማስወጣት ሂደት ላይ ነን” የራይድ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት

/ልዩ መረጃ– ከኤልያስ ጋር/

የራይድ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊትን የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ ይፋ ስላደረገው አዲሱ መመሪያ፦

“ሲጀመር የትራንስፖርት ቢሮው ይህን መመሪያ ማውጣት ይችላል ወይ የሚለው ላይ ጥያቄ አለ፣ ምክንያቱም እኛ የቴክኖሎጂ ድርጅት ስለሆንን የሚመለከተው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ነው።

በእኛ እምነት የትራንስፖርት ቢሮው ይህ ስልጣን የለውም። ሲቀጥል በRide ስር ከ 6,000 በላይ አባላት አሉ፣ የሚጎዱት እነዚህ ሰዎች ጭምር ናቸው። ይህ መመሪያ ሲወጣ እኛን ማሳተፍ ነበረበት። ሌላው ቀርቶ ረቂቁን እንኳን አላየነውም። በአጠቃላይ ይህንን ደንብ አንቀበለውም፣ ከፍርድ ቤት እገዳ ለማስወጣት ሂደት ላይ ነን።

በሌለ infrastructure አንድን ድርጅት እዚህ ማድረስ ቀላል አልነበረም። ይህንን ሁሉ ስራ ሰርተን እዚህ ስንደርስ appreciate መደረግ ነበረብን። በትራንስፖርት ቢሮ የተደረገው ግን እኛን የሚቃረን ነው።

እንደዚህ አይደረግም! ይህ ፈፅሞ መቆም ያለበት ነገር ነው። ይብቃ! ወጣቱ ይስራ! ሀገሪቱንም ያሳድግ! በዚህ አጋጣሚ ኢንጅነር ታከለ እና አቶ እንዳወቅ እየደገፉን ነው ያሉት። (የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮው) ዶ/ር ሰለሞን ግን ትንሽ ቆም ብለው አስበው ከእኛ ጋር ቢሰሩ ጥሩ ነው። ብዙ ልምድ አለን። ምን አልባት ልምድ የላቸውም ብለው አስበው ከሆነ ተሳስተዋል።”