ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የግብፅና የሱዳንን አዲስ ሀሳብ አልቀበልም አለች

በታላቁ የህዳሴ ግድብ የቴክኒካዊ አሰራርና የውሃ ሙሌት ቆይታ ዙሪያ ባደረጉት ውይይት መስማማት አልቻሉም፡፡

Egypt says GERD talks with Ethiopia ‘stumbled’, next round in Khartoum in October

http://english.ahram.org.eg/NewsContent/1/64/350910/Egypt/Politics-/Egypt-says-GERD-talks-with-Ethiopia-stumbled,-next.aspx

ባለፉት ሁለት ቀናት ፣ በሕዳሴው ግድብ ሙሌትና አተገባበር ላይ በግብጿ ካይሮ ላይ ሲመክሩ የነበሩት ሶስቱ አገሮች ውይይታቸውን መቋጨት አልቻሉም፡፡

ያልተቋጨውን ውይይታቸውን ለመቀጠል፣ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3/2012 ድረስ በሱዳኗ ካርቱም ተገናኝተው ለመምከር ተስማምተዋል፡፡

የግብፅን የመስኖ ልማት ሚኒስቴር መግለጫ ዋቢ አድርጎ አሕራም እንደዘገበው፣ በካይሮ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የቴክኒካዊ አሰራርና የውሃ ሙሌት ቆይታ ዙሪያ ባደረጉት ውይይት መስማማት አልቻሉም፡፡

የግብፅ መስኖ ልማት ሚኒስቴር እንደሚለው ከሆነ መስማማት ያልተቻለው ኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳንን አዲስ ሀሳብ አልቀበልም ስላለች ነው፡፡

“ስለዚህ” ይላል የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ “ስለዚህ ወገንተኝነት ከሌላቸው የባለሙያዎች ቡድን ጋር በካርቱም ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል”
በካርቱሙ ውይይት ግድቡ ስለሚሞላበት ሂደትና ስለሚቀረፁለት ህግ ግብፅ የምታቀርበው ሀሳብ ከባለሙያዎቹ ቡድን ጋር ይመከርበታል፡፡

የኢትዮጵያና የሱዳንም ሀሳቦች አብረው በቡድኑ ይታያሉ ተብሏል፡፡

ከገለልተኛ ኤክስፐርቶቹ ቡድን ጋር ከሚደረገው ውይይት በኋላም፣ የሶስቱ ሃገሮች የመስኖ ሚኒስትሮች በግድቡ የውሃ ሙሌት አተገባበርና ሕግ ላይ ለመምከር መስማማታቸውን የግብፅ የመስኖ ልማት ሚኒስቴር መግለጫ አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ሲመካከሩ 5 አመታት ማስቆጠራቸው ይታወሳል፡፡

ባለፉት ጊዜያት ንግግራቸው የህዳሴው ግድብን ለመሙላት ኢትዮጵያ የሶስት አመታት ጊዜ ስትወሰን ግብፅ ግን በሰባት አመታት እንዲራዘም ያላትን አቋም አጥብቃ ይዛለች፡፡

ወሬውን ያገኘነው ከግብፁ አሕራም ጋዜጣ ነው፡፡ Sheger FM