ኢጣሊያ ለችግር የተጋለጡ ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነች

ENA : ኢጣሊያ ተቀባይ አጥተው በባህር ዳርቻ ለችግር የተጋለጡ ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነች

የኢጣሊያ መንግስት ከሌሎች አውሮፓ መንግስታት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ 82 ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ ሆኗል፡፡

ስደተኞቹ በጀልባ ባህር አቋርጠው አውሮፓ ለመግባት ቢሞክሩም ተቀባይ ሀገር በማጣታቸው በባህር ዳረቻ ለቀናት ለመቆየት ተገደዋል፡፡

ኤኤፍፒ እንደዘገበው ኢጣሊያን ጨምሮ አምስት የአውሮፓ ሀገራት ስደተኞችን ለመከፋፈል ከስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ ላምፔዱሳ ደሴት በስተደቡብ የቆዩትን ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንደጊቡ ተደርጓል፡፡

ስደተኞቹ ከሮም ከባህር አድን ማስተባበሪያ ማዕከል ወደ ላምፔዱሳ እንዲንቀሳቀሱ መልእክት እንደደረሳቸውም ተመልክቷል፡፡

የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ክርሰቶፎር ካስታነር እንደገለጹት በኢጣሊያ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ፖረቹጋልና ሉዜምበርግ ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ሀገራት መካከል ይገኙበታል፡፡

” አሁን ጊዜአዊም ቢሆን ፍቱን መፍትሄ ለመስጠት የግድ ይለናልም ” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡