" /> የፌደራል መንግሥትና የተለያዩ ድርጅቶች በትግራይ ላይ ምጣኔ ሐብታዊ፣ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ጫናዎችን ለማሳደር በትግራይ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ሲያካሒዱ ነበር – ዶ/ር ደብረፅዮን | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የፌደራል መንግሥትና የተለያዩ ድርጅቶች በትግራይ ላይ ምጣኔ ሐብታዊ፣ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ጫናዎችን ለማሳደር በትግራይ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ሲያካሒዱ ነበር – ዶ/ር ደብረፅዮን

DW : የተገባደደዉ 2011 ዓመት ለትግራይ የሥጋትና የተስፋ ዓመት እንደነበረ የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ።

ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ደብረፅዮን ነገ የሚብተዉን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በተገባደደዉ ዓመት «ጥሩ» የሚባለዉ እርምጃ የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት መሻሻሉ ነዉ።

ከዚሕ ዉጪ ዓመቱ «ማንነት» ባሉት በጎሳ ጥቃትና ግጭት በየአካባቢዉ በርካታ ሕይወትና ሐብት የጠፋበት እንደነበር የትግራዩ መሪ አስታዉሰዋል።

ትግራይን በተመለከተ የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥት እና የተለያዩ ድርጅቶች በትግራይ ላይ ምጣኔ ሐብታዊ፣ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ጫናዎችን ለማሳደር «በትግራይ ላይ ያነጣጠረ «ዘመቻ ሲያካሒዱ ነበር» ብለዋል።

ዘንድሮ ከሰኔ አጋማሽ በኋላ የአማራ ገዢ ፓርቲ አዴፓና የትግራይ አቻና አጋሩ ሕወሓት በቃላት ሲወነጃጀሉ ነበር።ሁለቱ የኢሕአዴግ መስራች ፓርቲዎች የገጠሙትን እስጥ አገባ በመጪዉ ዓመት «በጠረጴዛ ዙሪያ» ዉይይት ለማስወገድ እንደሚጥሩ የአማራ ርዕሠ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነሕ አስታዉቀዉ ነበር።

የትግራዩ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ግን የአማራዉ ርዕሠ-መስተዳድር ለሰነዘሩት የድርድር ሐሳብ አሉታዊም-አወንታዊም አስተያየት አልሰጡም።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV