" /> የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን በዛሬው እለት ይፋ ተደረገ። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን በዛሬው እለት ይፋ ተደረገ።

Image result for የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

የ2012 መግቢያ ነጥብ!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን በዛሬው እለት ይፋ አደረገ።

በዚሁ መሰረት፦

በተፈጥሮ ሳይንስ •ለወንድ 176 •ለሴት 166

ማህበራዊ ሳይንስ •ለወንድ 174 •ለሴት 164

ለታዳጊ ክልሎች

√በተፈጥሮ ሳይንስ •ለወንድ 166 •ለሴት 156 √

በማህበራዊ ሳይንስ •ለወንድ 164 •ለሴት 154

ልዩ መቁረጫ ነጥብ

መስማት ለተሳናቸው

በተፈጥሮ እና በማህበራዊ ሳይንስ •ለወንድ 120 •ለሴት 115

አይነ ስውራን

በማህበራዊ ሳይንስ ብቻ •ለወንድ 110 •ለሴት 105

ለግል ተፈታኞች

በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ •ለወንድ 190 •ለሴት 185

አጠቃላይ ወደ ግል የትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር ለሚፈልጉ የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ ደግሞ 140 መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው ላይ እንዳስታወቀው፥ በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር 142 ሺህ 821 ነው።

የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ በአራት መሰረታዊ የትምህርት አይነቶች ውጤት መሠረት አድርጎ እንደሚወሰን መገለጹ ይታወሳል። የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥቡ የሚቆረጠው በእንግሊዝኛ፣ በሂሳብ፣ የስኮላስቲክስ አፕቲትዩድ፣ ከተፈጥሮ ሳይንስ በፊዚክስ ፣ ከማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በጂኦግራፊ የትምህርት ዓይነቶች ነው።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV