" /> አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የአማራ ክልል ጠ/ዐ/ህግ ገለጸ። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የአማራ ክልል ጠ/ዐ/ህግ ገለጸ።

በአማራ ክልል ለ4 ሺህ 329 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገለጸ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ገረመው ገብረጻዲቅ ለአብመድ እንደገለጹት፥ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ 5ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን አካሂዷል።

በስብሰባውም የ2012 ዓ.ም የዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ በክልሉ መንግስት ይቅርታ እንዲደረግላቸው በክልሉ ይቅርታ ቦርድ የቀረበለትን የይቅርታ ጥያቄ የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም የይቅርታ አሰጣጥ መስፈርቱን ያሟሉ 4 ሺህ 329 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ውሳኔ ማሳለፉን ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ገልጸዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ውስጥ 90ዎቹ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።

በሌላ በኩል ቀደም ሲል ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ ተላልፎላቸው እያለ ሌላ ወንጀል በመፈጸማቸው የተፈረደባቸው እና ማረሚያ ቤት የገቡ አምስት ታራሚዎች ተሰጥቷቸው የነበረው ይቅርታ ተሰርዞ ቀሪ የእስራት ጊዜያቸውን እንዲፈጽሙ ተወስኗል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV