አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ 1 ሺህ 87 የፌደራል ታራሚዎች በይቅርታ ይለቀቃሉ።

አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ 1 ሺህ 87 የፌደራል ታራሚዎች በይቅርታ ይለቀቃሉ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እንደገለፁት፥ በአዲሱ አመት 2012 ከሁሉም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በድምሩ 1 ሺህ 87 ታራሚዎች በይቅርታ ይለቀቃሉ።

ከዚህ ውስጥ 367 ከቃሊቲ፣ 28 ከዝዋይ እና 439ኙ ደግሞ ከሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ የሚለቀቁ ታራሚዎች በህግ ይቅርታ የማይጠየቅባቸው ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው በማረሚያ ቤት የቆዩ ናቸው።

(ኤፍ ቢ ሲ)


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE