" /> የመንግስት ግዴየለሽነት ለተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ንቅናቄ መስፋፋት ረድቷል ተባለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የመንግስት ግዴየለሽነት ለተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ንቅናቄ መስፋፋት ረድቷል ተባለ

DW : በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር ያለ አንድ ማህበር የኢትዮጵያ መንግስት በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ላይ አሳይቶታል ያለውን ዝምታ አወገዘ። ማህበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት የተሰኘው ይሄው ማህበር ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው መግለጫ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ መንግስት ጠንካራ ህግ ሊያወጣ ይገባል ብሏል።

የማህበሩ ሰብሳቢ መምህር ደረጀ ነጋሽ እንደተናገሩት መንግስት ለጉዳዩ ላይ ያለው ግዴየለሽነት ለተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ንቅናቄ መስፋፋት ረድቷል። ሰብሳቢው በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንዲስፋፋ የሚያደርጉት “የውጭ ዜጎች ናቸው” ሲሉም ወንጅለዋል። ለዚህም ዓላማቸው “እርዳታን፣ ፖለቲካን እና ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ” ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እስከ 15 ዓመት በህግ እንደሚያስቀጣ ቢደነገግም መምህር ደረጀ ግን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይበልጥ የጠነከረ ህግ እንዲያወጡ አሳስበዋል። ስሙ ያልተገለጸ አንድ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አክቲቪስት ለአሶሴትድ ፕሬስ እንደተናገረው በኢትዮጵያ ለሁኔታው ባለው የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ምክንያት “ለደህንነቴ እሰጋለሁ” ብሏል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV