" /> በእርግጥ ሕገ መንግሥቱ እና ፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ላይ ነው? – ውይይት | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በእርግጥ ሕገ መንግሥቱ እና ፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ላይ ነው? – ውይይት

DW : ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አደጋ ላይ ነች የሚሉ ማሳሰቢያዎች መሰማት ከጀመሩ ውለው አደሩ። ይህን የሚሉት ወገኖች የተለያዩ መንስኤዎችን በማንሳት ነው ሀገር አደጋ ላይ ናት የሚሉበትን ስጋት ለማሳየት የሚሞክሩት። ለአንዳንዶቹ ሕገ መንግሥቱ የአደጋ ምንጭ ነው፤ ለሌሎቹ ደግሞ ይኸው ሕገ መንግሥት ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የሕልውና መሠረት ነው። ሕገ መንግሥቱ ከተነካም ለአደጋው ምንጭ ሊሆን እንደሚችልም ያሳስባሉ። ከሰሞኑ ሕገ መንግሥቱ እና ፌደራላዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለማዳን በሚል መቀሌ ላይ የሁለት ቀናት ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር። ራሱ ያላከበረውን ሕገ መንግሥት ከአደጋ ለማዳን ጥሪ በማቅረብ ሀገሪቱን ላለፉት 27 ዓመታት የመራው ግንባር ተጠያቂ የሚያደርጉም አሉ። በእርግጥ ሕገ መንግሥቱ እና ፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ላይ ነው? ዶቼ ቬለ ባካሄደው ውይይት ላይ ለዚህ ስጋት መንስኤ የሆኑት ማመላከቻዎች እና ከአደጋ እናድነው የሚለውን ጥሪ የተቹ ወገኖች ተሳትፈዋል።

ሙሉ ውይይቱን ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV