ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እድሳት ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እድሳት ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በክረምት ለተደረገለት እድሳት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በዘንድሮው ክረምት እድሳት ሲደረግለት በበጎ ፈቃደኝነት ገንዘብ ለለገሱ ባለሃብቶች እውቅና ሰጥተዋል።

ሌሎችም የነዚህን በጎ ፈቃደኞች አርአያ በመከተል ህዝብን በነፃ የማገልገልና የመደገፍ ተግባር ባህል እንዲያደርጉ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጴጥሮስ ሆስፒታል ያስገነባውን አዲስ ህንፃም በዛሬው እለት መርቀዋል።

የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እንዳሉትም በጥቁር አንበሳ የተደረገው በጎ ተግባር ለሌሎች ሆስፒታሎችም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው።

ENA


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE