ጠ/ሚ አብይ በሱዳን እስር ቤቶች የነበሩ ኢትዮጵያዊንን በመያዝ አዲስ አበባ ገቡ

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በሱዳን እስር ቤቶች የነበሩ ኢትዮጵያዊንን በመያዝ በአዲስ አበባ ገቡ

Image may contain: one or more people, people standing and outdoor

ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር አብይ አህመድ በሱዳን እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጰያዊያንን በመያዝ አዲስ አበባ ገቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ፈርማ ስነ ስርዓት አጠናቀው ሲመለሱ ነው ኢትዮጵያዊያኑን በመያዝ አዲስ አበባ የገቡት፡፡ኢትዮጵያኑ በተለያዩ ምክንያቶች በሱዳን እስር ቤቶች የነበሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

Image may contain: one or more people and outdoor
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት በአዳራሹም ሆነ በጎዳናዎች የነበሩ ሱዳናዊያን ለኢትዮጵያና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ምስጋና ሲያቀርቡ ነበር፡፡የሱዳን የፓለቲካ ሀይሎች በደረሱት በስምምነቱ መሰረት የልዑላዊ ምክር ቤት የሚቋቋም ሲሆን ምክር ቤቱ ስድስት የሲቪል እና አምስት ወታዳዊ አመራሮችን በአባልነት ያካታል፡፡

Image may contain: 3 people, people standing
የልዑላዊ ምክር ቤቱን ሁለቱ ወገኖች በየሶስት ዓመት እየተፈራረቁ የሚመሩት ሲሆን በዚህ መሰረት ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የነፃነትና የለውጥ ሀይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚሾም ይሆናል፡፡በዚህ ስምምነት ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩል ከፍተኛ ሚና እንደነበራት የገለፀ ሲሆን ለዚህም ሱዳናዊያኑ ምስጋና አቅርበዋል::

(ኤፍ ቢ ሲ)

Image may contain: 3 people, people standing and outdoor