በደቡብ ክልል ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለስ ተችሏል- ኮማንድ ፓስቱ

በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የነበረውን አለመረጋጋት የአካባቢውን ህብረተሰብ በማሳተፍ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ፡፡

Image may contain: 4 people, people sitting and indoor

ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ በሀዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመቆጣጠር የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ያከናወናቸውን አበይት ተግባራት አፈጻጸም ዛሬ ገምግሟል፡፡
በግምገማውም በሀዋሳና በሲዳማ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የተዘረፉ ንብረቶችን ህብረተሰቡን በማሳተፍ ማስመለስ የተቻለ ሲሆን በግጭቱ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬ አቸው እዲመለሱ ተረደርጓል ብሏል፡፡

እንዲሁም የተሰባበሩ ቤቶች እና ንብረቶች እንዲጠገኑ መደረጉንም ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡

ኮማንድ ፓስቱ በሀዋሳ ከተማ ፣ በሲዳማ ዞን እና በክልሉ አንዳንድ ዞኖች በህገወጥ መንገድ የተሰቀሉ ሰንደቅ አላማዎች እና ታፔላዎች ወርደው በምትኩ ህጋዊ ሰንደቅ አላማዎች እና ታፔላዎች እንዲሰቀሉ ማድረጉን ከከልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ህገ ወጥ የወጣት አደረጃጀቶች ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገቡ የተጀመረው ስራ አበረታች መሆኑን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡

ሀምሌ 11 ቀን 2011 ዓም በነበረው የጸጥታ ችግር ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉት 1 ሺህ 384 ሰዎች ውስጥ የማጣራት ስራ በመስራት 481 ተጠርጣሪዎች የተለቀቁ ሲሆን ቀሪ 903 ተከሳሾች በክስ ሂደት ላይ መሆናቸውን ኮማንድ አስታውቋል፡፡

Source – FBC