በከተሞች የድምፅ ብክለት መጠናቸው እየጨመረ መጥቷል ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞች የድምፅ ብክለት መጠናቸው እየጨመረ መጥቷል ተባለSheger FM

የሃይማኖት ተቋማት፣ ማምረቻዎች፣ ትራንስፖርትና የንግድ ተቋማት በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ብክለት ያስከትላሉ ተብለው የተለዩ ዘርፎች ናቸው፡፡የህዝብ ቁጥር መጨመርና የከተሞች መስፋፋትም ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ለመጣው የድምፅ ብክለት ምክንያት መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡የአካባቢ ደህንነትና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ይህንኑ በዜጎች ጤናና አኗኗር ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰውን የድምፅ ብክለት ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ማዘጋጀቱን ተናግሯል፡፡

ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት፣ ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ባለድርሻዎች በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት እያደረጉ ሲሆን ደንቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀ የድምፅ ብክለትን ለመከላከል ከፍ ያለ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡በረቂቅ ህጉ የድምፅ ብክለትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት የሚቻልበት አሰራር የተካተተ ሲሆን በተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መሰረት ይተገበራል ተብሏል፡፡

sheger FM