የሲዳማ ዞን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ክልልነት የህዝበ ውሳኔ ቀን ይፋ እንዲያደርግ ጠየቀ

DW : የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበትን የህዝበ ውሳኔ ቀን ይፋ እንዲያደርግ የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ጠየቀ።

ምክር ቤቱ ትናንት ለአንድ ቀን ሀዋሳ ላይ በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ቦርዱ ህዝበ ውሳኔውን ገቢራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መጀመሩ መልካም ቢሆንም ውሳኔው የሚካሄድበትን ትክክለኛ ቀን ግን ከወዲሁ ሊያሳውቅ ይገባል ብሏል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም አቶ ደስታ ሌዳሞ በቅርቡ ከኃላፊነታቸው የተነሱትን አቶ ቃሬ ጫውቻን በመተካት ዞኑን በዋና አስተዳዳሪነት እንዲመሩ የቀረበውን ሹመት በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል።