ታይቶ የማይታወቅ ነው የተባለ የውሐ መጥለቅለቅ አደጋ በጎንደር ተከሰተ

DW : በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን የርብና ጉማራ ወንዞች ከገደፋቸው አልፈው በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳደር አስታወቀ።ነዋሪዎች እንደሚሉት በዞኑ በሊቦከምከም እና በፎገራ ወረዳዎች የሚገኙ 6 ቀበሌዎች በውኃ በመጥለቅለቃቸው የአካባቢው ህብረተሰብ የሚበላው አጥቷል።

እስከ ዛሬ ታይቶ የማይታወቅ ነው በተባለው በዚህ አደጋ እርሻዎች በውኃ ተጥለቅልቀዋል፣የእንሰሳት የመኖ አቅርቦት ችግርም ተከሰቷል። በአካባቢው ቀደም ሲል ርብ ወንዝ ላይ የተገነባው የመስኖ ግድብ ለወንዙ ከመጠን በላይ መሙላት አንዱ ምክንት ነው ተብሏል።ከሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ በአካባቢው እየጣለ ያለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የወንዞች ሙላት በደቡብ ጎንደር በሚገኙ የሊቦከምከምና ፎገራ ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እደረሰ እንደሆነ የአካባቢው ባለስልጠናት ለዶቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡ አካባቢውን የሚያውቁትና የደብረታቦር ከተማ ነዋሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ እንዳሉት

Überflutung inSüd- Gondar ( Biruk Teshome ) የርብና የጉማራ ወንዞች ታይቶ በማታወቅ ሁኔታ በመሙላታቸውና ገደባቸውን አልፈው በመፍሰሳቸው በሁለቱም ወረዳዎች ከ6 በላይ ቀበሌዎችን አጥለቅልቀዋል፡፡ ከቀበሌዎቹ እስከ 500 አባወራዎቸ ይኖሩባቸው እንደነበርም አስረድተዋል፡፡የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በበኩላቸው በተለይ የርብ ወንዝ መጠኑ የጨመረው በአካባቢው ካለው ግድብ ጋር የተያያዙ ማፋሰሻዎች በመደፈናቸው መሆኑን ጠቁመው ነዋሪዎቹ በከፋ ሁኔታ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያና ልዩ ደጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ኤጀንሲ ኮሚሽነር  አቶ አማረ ክንዴ እንዳሉት በተጥለቀለቁ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎችን ወደ ደረቅ ቦታ ለማስፈር ጀልባዎችና ድንኳኖች ወደ አካባቢው መለካቸውን አመክክተዋል፡፡ሥራው በሂደት ላይ በመሆኑ የተፈናቃዩን ቁጥር አሁን ማወቅ እንደማቻልም አቶ አማረ አስረድተዋል፡፡በተመሳሳይ በዋግኽምራ ዞን ዝቋላ ወረዳን ከሳህላ ሰየምት የሚያገናኘው የተከዜ የብረት ድልድይ በወንዙ ሙላት በመዋጡ የሁለቱ ወረዳዎች የትራንስፖርት ፍሰት መስተገዋጎሉን የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ባለሙ አቶ መብራቱ መኮንን ለዶይቼ ቬለ በስልክ አስታውቀዋል፡፡