በመተከል ዞን ታዳጊው ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡

በመተከል ዞን ታዳጊው ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡

በመተከል ዞን ዲባጢ ወረዳ በአንድ የአማራ ተወላጅ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌ በልጋፎ ተናገሩ፡፡

የተሰራው ወንጀል ወረዳውን እንዳሳዘነ አቶ ደበሌ ገልፀው እንደዚህ አይነት ችግሮች ዳግም እንዳይፈጠሩ ማህበረሰባዊ ውይይቶችን እያደረግን ነው ብለዋል፡፡የተጠርጣሪዎችን የምርመራ ውጤትም ለህዝብ እንገልፃለን ብለዋል፡፡

የ 14 ዓመቱ ተጎጂ አበጠር ወርቁ አጎት አቶ አያሌው አበረ በበኩላቸው በወንድማቸው ልጅ ላይ የደረሰው አስነዋሪ ድርጊት እንዳሳዘናቸው ገልፀው፣ተጎጂው ለህክምና ከፓዊ ወደ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል እንደገባ አረጋግጠውልናል፡፡

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌም ለከፍተኛ ህክምና ወደ ባህርዳር እንደሚሄድ ቀደም ብለው ያረጋገጡ ሲሆን፣ወረዳው ከተጎጂው ጎን ይቆማልም ብለዋል፡፡
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቱን ለማጥፋትም እንደሚሰራ ተገልጧል፡፡
በዲባጢ ወረዳ የአማራ፣የኦሮሞ፣የጉምዝ፣የሽናሻ ወ.ዘ.ተ ህዝቦች በጋራ እንደሚኖሩ አቶ ደበሌ ተናግረዋል ፡፡

የሺሀሳብ አበራ