የገንዘብ ኖት መጠን በየአመቱ በ27% ሲያድግ ቆይቷል

ከ11* አመታት በፊት በአገራችን በዝውውር ውስጥ የነበረው የገንዘብ ኖት 68 ቢሊየን ብር እንደነበረ ያስታወሱት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ አሁን ወደ 740 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡ የገንዘብ ኖት መጠንም በየአመቱ በ27% ሲያድግ ቆይቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ያለፉት አመታት የኢኮኖሚ እድገት በአብዛኛው በብድርና በገንዘብ ማተም የመጣ ነው ተባለ

በዚህም ምክንያት አጠቃላይ ኢኮኖሚው ተናግቶ መቆየቱ ተነግሯል፡፡የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እና “በኢኮኖሚው ውስጥ የመንግስት ሚና” በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡በውይይቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ እንዳሉት ባለፉት አመታት የኢኮኖሚ እድገት ተመዘግቧል ቢባልም እድገቱ በአብዛኛው በብድርና በገንዘብ ማተም የመጣ ነው፡፡እድገቱ በአገራችን ያለውን የድህነት መጠን እምብዛም ያህል እንዳልቀነሰም ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት መንግስት ከውጪ የተበደረው የዕዳ መጠን አሁን 29 ቢሊየን ዶላር ያህል ነው፡፡ከአገር ውስጥ የወሰደው ብድርም ከዚህ እንደማይተናነስ ተናግረዋል፡፡ከ27 አመታት በፊት በአገራችን በዝውውር ውስጥ የነበረ የገንዘብ ኖት 68 ቢሊየን ብር እንደነበረ ያስታወሱት ፕሮፌሰር አለማየሁ አሁን ይህ መጠን 740 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡የገንዘብ ኖት መጠኑ በየአመቱ በ27 በመቶ ሲያድግ ቆይቷል ብለዋል፡፡

የገንዘብ ኖት እድገቱ፣ መሆን ከነበረበት 4 እና 5 እጥፍ የበለጠ እንደሆነ ፕሮፌሰር አለማየሁ አክለዋል፡፡ክስተቱ ከፍተኛ የብር ኖት እየታተመ ለዝውውር ይበቃ እንደነበር ያሳያል ብለዋል፡፡መንግስት ባለፉት 10 አመታት በልማታዊ መንግስት ቅኝት ከፍ ያለ መዋዕለ ነዋይ በመሰረተ ልማት ላይ እንደዋለም ተናግረዋል፡፡የኢኮኖሚ እድገቱ መዋቅራዊ ለውጥ እንዳላመጣም በምክክሩ ወቅት ተነስቷል፡፡ለዚህም አገሪቱ ከደካማ ምርታማነት አለመላቀቋ በማጠቃሻነት ተጠቅሷል፡፡በማህበራዊ የጥናት መድረክ አዘጋጅነት በተጠራው ውይይት ላይ ተጨማሪ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ነው፡፡

Source : ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US