በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ ።

በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ ።

ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባና በባህርዳር ከተሞች ከመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በባህርዳር ከተሞች ከመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ፣ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።

ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ባቀረው የጊዜ ቀጠሮ ላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቶበታል።

በዚሁ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡት 1ኛ በሪሁን አዳነ፣ 2ኛ መርከቡ ኃይሌ ፣ 3ኛ ስንታየሁ ቸኮል፣ 4ኛ ጌዲዮን ወንድወሰን፣ 5ኛ ማስተዋል አረጋ እና 6ኛ ኃየሎም ብርሃኔ ናቸው።
( ኢዜአ )


► መረጃ ፎረም - JOIN US