ደቡብ ክልል የተላከ ከጅቡቲና ከሱዳን የተነሳ 16 ቦቴ የነዳጅ ምርት የት እንደደረሰ አይታወቅም

ዶቼ ቬለ  – በደቡብ ክልል በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚካሄደው የጥቁር ገበያ ንግድ የምርት አቅርቦትና ስርጭትን አያስተጓጎለብኝ ነው ሲል የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አማረረ። ለክልሉ እንዲደርስ ተብሎ ከጅቡቲና ከሱዳን የተነሳ አስራ ስድስት ቦቴ የነዳጅ ምርት አስከአሁን የደረሰበት አለመታወቁን አንድ ከፍተኛ የቢሮው ኃላፊ ለዶቼ ቬለ ( DW ) ተናግረዋል። የኢትዮጲያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በበኩሉ ችግሩ ሊባባስ የቻለው የስራ ፍቃድ ሰጪው የፌደራል ንግድ ሚንስቴር የነዳጅ ምርቶችን ከመዳረሻ የማደያ ጣቢያዎች ውጪ በሚያራገፉ ኩባንያዎች ላይ ተገቢውን ቁጥጥርና እርምጃ ባለመወሰዱ ነው ይላል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US