በጂማ ሊሙ ሦስት አማሮች ሌሊት ላይ በገጀራ ታርደዋል

በጂማ ሊሙ ዛሬ የሚከበረውን የክርስቶስ እርገት ለማክበር በማታ ወደ ጨንጊ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ላይ የነበሩ ሦስት የአማራ ተወላጆ በገጀራ ታርደው የተገደሉ ሲሆን አንድ ሰው በከባድ ጉዳት ሕክምና ገብቷል፡፡

ሁሉም የተገደሉት የገብረ መንፈስ ቅዱስ ማኅበርተኞች ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በ1999 ዓም በርካታ አማሮች በሻሻ አቦ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በገጀራና በእሳት መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ሀብታም የሆኑ የአማራ ተወላጆች በብዛት እየተገደሉ ነው፡፡

ትናንት በገጀራ ታርደው የተገደሉት ስም ዝርዝር

1. አስማማው አማረ
2. መርሻ መኮንን
3. መኳንንት

የተባሉ ሲሆን የቆሰለው ብርሀኑ ጌቱ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶበታል፡፡