በደቡብ ክልል ከ40 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው ተሰማ

DW : በ2011 ዓ.ም. በደቡብ ክልል በነበረው አለመረጋጋት በጉራጌ፣ ሲዳማ፣ በከፋ፣ በጎፋ እና በጌድዖ አካባቢዎች ከ50 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በመዘጋታቸው ከ40 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በክልሉ ሰባት ትምህርት ቤቶች መቃጠላቸውንም ኃላፊው ገልጸዋል

በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ላለፈው አንድ ዓመት ሙሉ በሙሉ ተዘግተው የነበሩ ሃምሳ ትምህርት ቤቶችን አገልገሎት ለማስጀመር የሚስችለውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ ዛሬ ከዶቼ ቨለ ( ዲ ደብሊው ) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት በክልሉ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ከአርባ ሺህ በላይ ተማሪዎችንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በክልል በተለያዩ አካላት የሚነሱ ፖለቲካዊ የመብት ጥያቄዎችና የተቃውሞ ሰልፎች የትምህርት ስራን በማይነካ መልኩ በራሳቸው መስመር ብቻ መስተናገድ እንደሚገባቸው ከማህበረሰቡ ጋር መግባባት ተፈጥሯል ብለዋል።

Image result for south ethiopia schools


► መረጃ ፎረም - JOIN US