በደቡብ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት ማለፉን እና ንብረትም መውደሙን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ

ዶቼቬለ – በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት ማለፉን እና ንብረትም መውደሙን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ። የዓይን ምስክሮቹ በተለይ በሞሮቾ በሃገረ ሰላም በአለታ ወንዶ እና በይርጋለም ከተሞች የሲዳማ ክልልነት በይፋ እንዲታወጅ በሚጠይቁ ወጣቶች እና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ከትናንት ጀምሮ በተፈጠረው በዚሁ ግጭት በተለይ በሞርቾ እና በሃገረ ሰላም ከተሞች ከሞቱት መካከል አብዛኛዎቹ ታዳጊ ወጣቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል።በግጭቱ የግለሰቦች እና የመንግሥት መኪናዎች መቃጠላቸውንም ተናግረዋል።

እንደ ዓይን እማኞቹ በተለይ በሞሮቾ አውራ ጎዳናዎች በድንጋይ በመዘጋታቸው ከሃዋሳ ወደ ይርጋለም ፣አለታ ወንዶ እና ሃገረ ሰላም የሚያገናኙ የትራንስፖርት አገልግሎቶች መቋረጣቸውንም የዓይን እማኞች ገልጸዋል።በሃገረ ሰላም ከተማም ወጣቶች የግለሰቦች እና የመንግሥት ንብረት ሲሰብሩ እና ሲቃጥሉ እንደነበርም እነዚሁ የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

አለመረጋጋቱ በተስፋፋባቸው የሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች እስካሁን በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት መጠን ከክልሉም ሆነ ከሲዳማ ዞን የፀጥታ አካላት ማረጋገጥ አልተቻለም። ዶቼቬለ DW ያነጋገራቸው የሲዳማ ዞን የስራ ሃላፊዎች በከተሞቹ ሰዎች መሞታቸውን እና ንብረት መውደሙን ቢያረጋግጡም ዝርዝር መረጃ እየጠበቁ መሆናቸውን እንደተናገሩት ዶቼቬለ ዘግቧል።

An armed security officer roams on an empty street during a clash between a Sidama youth and securities after they declared their own region in Hawassa, Ethiopia July 18, 2019.

ተጨማሪ ዘገባ

Read More https://www.telesurenglish.net/news/Four-Killed-As-Protests-Spread-in-Southern-Ethiopian-City-20190719-0015.html