ክልል ለመሆን በኃይልና በዛቻ ለማስፈጸም የሚደረገውን እንቅስቃሴ ብዙዎች እየተቃወሙት ነው

DW : በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ አቀራረብ፣ እና በምርጫ ቦርድ መልስ እንዲሁም በጥያቄው አተገባበር ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰማሉ። ክልል የመሆን ጥያቄ ማቅረብ መብት ስለ መሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ።ሆኖም ጥያቄውን በኃይል እና በዛቻ ለማስፈጸም የሚደረገውን እንቅስቃሴ ግን ይቃወማሉ።አስተያየት ሰጭዎቹ ጥያቄ አቅራቢዎቹ ሃገሪቱ የምትገኝበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ታግሰው እንዲጠብቁ ይመክራሉ።