አምንስቲ ኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት በማክበር ረገድ ባለፈዉ አንድ ዓመት ያሳየችዉ መሻሻል እንዳይቀለበስ አሳሰበ።

DW : ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት በማክበር ረገድ ባለፈዉ አንድ ዓመት ያሳየችዉ መሻሻል እንዳይቀለበስ አሳሰበ።የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ትናንት ባሰራጨዉ መግለጫዉ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማሰሩና ለመክሰስ ማስጠንቀቁ ሐገሪቱን ከዓመት በፊት ወደነበረችበት እንዳይመልስ ያሰጋል ባይ ነዉ።ድርጅቱ የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ፣ የተመሠረተባቸዉ ክስም እንዲቋረጥ ጠይቋልም።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE