ኢሕአዴግ ኮማ ውስጥ ነው ! (ምኒሊክ ሳልሳዊ)

ኢሕአዴግ ኮማ ውስጥ ነው ! (ምንሊክሳልሳዊ )

ለሐገሬ የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀምጫለሁ ያለው ኢሕአዴግ የአቅጣጫው ቀለም ሳይደርቅ ወደ መፈረካከስ እያመራ መሆኑን ሕወሓት በመግለጫው አጋልጧል።

ሕወሓት በመግለጫው ብአዴን / አዴፓ በሶስተኛ አካል ማሳበብ ትቶ ዉስጡን በጥልቀት እንዲፈትሽና እንዲገመግም ለኢትዮጵያ ህዝቦች ይቅርታ እንዲጠይቅ ካልሆነ ግን ህወሓት ከአዴፓ ጋ መስራት እንደማይችል ገለጸዋል ።

ኦሕዴድ ኦዴፓ ኢሕአዴግን አንድ ለማድረግ ያቀደው ሐሳብ በመኮላሸቱ እና አብዛኛው መዋቅሩ በኦነግ በመጠለፉ አጣብቂኝ ውስጥ ነው ።አዴፓም የውስጥ አደገኛ ሽኩቻው ከሕዝብ ጥላቻና ከሰሞኑ ሴራ ጋር ተደማምሮበት በፓለቲካ ስካር እየተሰቃየ ነው።

ሌላኛው የደቡቡ ፓርቲ የኢሕአዴግ አጋር በደቡብብ ክልል በተነሱ የክልል እንሁን ጥያቄዎች ለመበታተን ተቃርቧል። በተቀመጠው ስብሰባ ላይ ከባድ ልዩነት እየጦዘ ስለሆነ ኦዴፓ እጁን አስገብቶ የደቡብን ፖለቲካ እያማሰለው ፓርቲውን በጣር እያስቃሰተው ነው።

ሕወሓት የመከላከያ ሰራዊት ሐገርን ከመፍረስ እንዲያድን ጥሪ ሲያቀርብ ኢሕአዴግ ኮማ ውስጥ እንደሆነ በመግለጫው መስክሯል ። የሀገራችን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ የኢሕአዴግን እድሜ እንደሚያሳጥረው ከወዲሁ በፈጣሪው ሕወሓት መግለጫ ውስጥ አንብበናል።
#MinilikSalsawi


► መረጃ ፎረም - JOIN US