ሕወሓት የንግድ ኩባንያ ሼሮች ለግል ባለሀብቶች ሊሸጥ ነው

ሶስት የትእምት ኩባንያ ሼሮች ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ

የመሰቦ ሲሜንቶ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽንና የትራንስ ኢትዮጵያ ሼሮች ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉን የትግራይ ክልል አስታወቀ፡፡

በምክትል ርእሰ መስተዳድር መዓርግ የትግራይ ክልል የከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብርሃም ተኸስተ በሰጡት መግለጫ፥ የትግራይ ክልል ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በኩባንያዎቹ በተዘጋጀው የሼር ሽያጭ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ባለሀብቶች ያዘጋጇቸው የሶስት ኩባንያዎች ሼር ሽያጭ በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ በሚዘጋጀው ዓለም አቀፋዊ የትግራይ ዳያስፖራ ፌስቲቫል ወቅት ለሽያጭ ለማቅረብ አስፈላጊውን ዝግጅት መጠናቀቁ ዶክተር አብርሃም አስታውቀዋል።

ይህንን እቅድ ውጤታማ ለማድረግ ከዚህ ቀደም ሲታዩ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት ባለ ሀብቶች ቀጥታ ወደ ኢንቨስትመንት ማስገባት የሚያስችል ስራ እንደተከናወነም ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የግል ኩባንያ በማቋቋም በክልሉ ባለው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉም ነው የተነገረው።

ስለሆነም ባለሀብቶች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በሟሟላት ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸውም ዶክተር አብርሃም በመግለጫቸው አሳስበዋል።

Source FBC


► መረጃ ፎረም - JOIN US