አትሌት ደራርቱ ቱሉ በኢጣልያ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ሽልማት ዕውቅና ተሰጣት

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በኢጣልያ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ሽልማት ዕውቅና ተሰጣት

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በኢጣልያ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ሽልማት የህይወት ዘመን የስፖርታዊ ጨዋነት ዘርፍ ተሸላሚ ሆነች።

ሽልማቱ ኢጣልያ በሚገኝ ”ፕሪሞ ኢንተርናሽናል ፌር ፕሌይ” በተሰኘ ድርጅት በስፖርቱ ታሪክ የሰሩ፣ በታማኝነት የተወዳደሩ እና ዘርፉን ያገለገሉና ስፖርትን በማስፋፋት ታሪክ ለሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና የሚሰጥበት ነው።

በዚህ ዓመት ለ23ኛ ጊዜ ሽልማትና ዕውቅና የተሰጠ ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከተሸላሚዎች መካከል ተመርጣለች።

አትሌት ደራረቱ ቱሉ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1992 ባርሴሎና በተካሄደ የኦሎምፒክ ውድድር በ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ በመሆን የመጀመሪዋ አፍሪካዊት ሴት አትሌት ናት።

ከዚህ በተጨማሪ በአትሌቲክስ ስፖርት ረጅም ጊዜ በውድድር በቆየችባቸው ዓመታት ናቸው የህይወት ዘመን የስፖርታዊ ጨዋነት እውቅና ያሰጧት።

አትሌት ደራርቱ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በበላይነት እየመራች ሲሆን የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ የአካባቢው ምክትል ፕሬዚዳንትም ናት።

ከአትሌት ደራርቱ ቱሉ በተጨማሪ የቀድሞ የኢጣልያ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች አንቶኒዮሪቫ ተሸላሚ ሆኗል።

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በኢጣልያ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ሽልማት ዕውቅና ተሰጣት