የተፈናቀሉ 50 ሺህ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመልሶ ማቋቋምና ማገገም ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

የተፈናቀሉ 50 ሺህ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመልሶ ማቋቋምና ማገገም ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

በጌዴኦና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ 50 ሺህ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመልሶ ማቋቋምና ማገገም ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ ፡፡

በተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም አስተባባሪነት የሚከናወነው ይህ ፐሮጀክት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ይፋ የተደረገ ሲሆን 20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቅ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀው መርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ዋና ኃላፊ ሚስተር ቱርሀን ሳሌህ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በዋናነት በጌዴኦና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ከደረሰባቸው ጉዳት አገግመው ወደ መደበኛ ኑሯቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ያለመ ነው ፡፡

በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት የደረሰባቸው 50 ሺህ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ይህ ፕሮጀክት 20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን በአራት ዓመታት ውስጥ እንደሚከናወን አመልክተዋል ፡፡

“በመጀመሪያው ዓመት አምስት ሚሊዮን ዶላር በሚጠጋ ገንዘብ ከአምስት ሺህ ቤተሰቦች በላይ ድጋፍ ይደረግላቸዋል” ብለዋል፡፡

ለዚህ ማስፈፀሚያ የሚውል ከጃፓን መንግስት 1 ሚሊዮን ዶላር ከዴንማርክ መንግስት ደግሞ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ተገኝቷል ፡፡

የተፈናቀሉ 50 ሺህ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመልሶ ማቋቋምና ማገገም ፕሮጀክት ይፋ ሆነ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE