የኤርትራና የኢትዮጵያ ታሪካዊ የሰላም ስምምነት አመት ሞላው።

የኤርትራና የኢትዮጵያ ታሪካዊ የሰላም ስምምነት አመት ሞላው። ለአስርት አመታቶች የዘለቀው የሁለቱ ሃገራት የጦርነት ነጋሪት ቆሞ በዶክተር አብይ የሚመራው መንግስት ከ ኤርትራው ፕሬዝዳንት ጋር በተስማማው መሰረት ሁለቱ ሃገራት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

Image

ከስምምነቱ በመቀጠል ሃገራቱ ድንበሮቻቸውን ክፍት አድርገው የተለያየ የንግድ ልውውጦች ጀምረው የነበረ ቢሆንም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ በድንበር መከፈቱ ተቆራንቶ የነበረ ቢሆንም የኮንትሮባንድና የሕዝብ ፍልሰትን ተከትሎ የ ኤርትራ መንግስት ዳግም ድንበሩን መዝጋቱ ይታወሳል።

በድንበር አከባቢ ያሉ ዜጎች የድንበሩ መዘጋት ቢያስቆጣቸውም የተለያዩ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ አለመሆኑ እንደሚያሳስባቸው በተለያዩ መድረኮች ገልጸዋል።አሁንም የሁለቱ አገራት ስምምነት ወደ ሕዝብ ወርዶ የተረጋገተ እርቀ ሰላም እንዲመጣ እየተጠየቀ ይገኛል።

ኤርትራ የድንበር መዘጋቱን ጉዳይ በተመለከተ ዝምታን መርጣለች ።የ አሰብ ወደብ በኢማራቶች በሊዝ መያዙና ኢትዮጵያ በወደቡ የመጠቀሟ ሕዝብ ለ ኤርትራ የተዋጠላት ስላልሆነ ወደቡ ስራውንም አልጀመረም። የድንበር መዘጋቱ በተመለከት ኢትዮጵያ ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የተደረገ እንደሆን አስታውቃ ነበር።#MinilikSalsawi

https://www.aljazeera.com/indepth/features/peace-uncertainty-ethiopia-eritrea-deal-190708115216882.html


► መረጃ ፎረም - JOIN US