መከላከያ ሰራዊት በተሰማራባቸው አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም ማስፈን መቻሉ ተገለፀ

መከላከያ ሰራዊት በተሰማራባቸው አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም ማስፈን መቻሉ ተገለፀ ።

የመከላከያ ሰራዊቱ የፀጥታ ችግር በተከሰተባቸዉ አካባቢዎች ላይ በመሰማራት አካባቢዎቹ ወደሰላም እንዲመለሱና ህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዉን እንዲሁም የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ ረገድ ባከናወናቸዉ ተግባራት አንፃራዊ ሰላም መፍጠር መቻሉ ተገለፀ፡፡

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሃመድ ተሰማ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታንና የሰራዊቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ አስመልከቶ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት ያለፈዉ የበጀት አመት ሃገራዊ ለወጡን ተከትሎ በተቋም ደረጃ የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች የሰራዊቱን የመፈፀም አቅም የሚያሳድጉ ዉሳኔዎች የተላለፉበት አመት ነበር፡፡

በአጎራባች ክልሎች፤ በሜጋ ፕሮጀክቶችና የተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ የፀጥታ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ከአካባቢዉ ህብረተሰብና ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር ዉጤታማ ስራዎች መከናወናቸዉንም አመልክተዋል፡፡

የሰራዊቱን ስም የማጥፋት ዘመቻዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ እንደሚገኙና ይህም ዘመቻ ሰራዊቱን በዘር ለመከፋፈል ያለሙና የአገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ የዉጭ ሃይሎችና ተላላኪዎቻቸዉ የሚፈፀም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ተቋሙ በአገሪቱ ህግ መሰረት ስሙን የማጠልሸት ዘመቻ ላይ የሚሳተፉ አካላት ላይ ተገቢዉን እርምጃ እንደሚወስድም ተናግረዋል፡፡

ስም የማጥፋት ዘመቻዉ በፀጥታ ማስከበር ስራዉ ላይ እክል እየፈጠረ በመሆኑ ይህን የሚያደርጉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡም ጠይቀዋል፡፡

Fana tv


► መረጃ ፎረም - JOIN US