ኢኮኖሚው በሚቀጥለው የበጀት ዓመት 9 በመቶ እድገት እንዲያስመዘግብ ታስቧል ተባለ።

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚቀጥለው ዓመት የቀረበው የ387 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ረቂቅ ላይ ዛሬ ተወያየ። ባሳለፍነው ቅዳሜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ በጀቱ ላይ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። የገንዘብ ሚንሥትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ዛሬ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የበጀት ዝርዝር ላይ ውይይት ተካሂዷል። ለ2012 ዓም የተያዘው በጀት ባለፈው ዓመት ከጸደቀው በጀት የ1 ነጥብ 6 ጭማሪ እንዳለው ሚንሥትሩ ተናግረዋል። ኢኮኖሚው በሚቀጥለው የበጀት ዓመት የተወሰነ መነቃቃት በማሳየት ከዘጠኝ በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ታሳቢ መደረጉንም አክለው ገልጠዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE