ህብረተሰቡ የፓልም ዘይትን እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ!

አብመድ

ህብረተሰቡ የፓልም ዘይትን እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ!

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተለያዩ የምግብ ዘይቶች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ጥናቱን ዛሬ ሰኔ 5/2011 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው ይፋ ያደረገው፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ እንደገለፁት በፈሳሽ እና በሚረጉ ዘይቶች ላይ ጥናት ተደርጓል፡፡ በሚረጉ ዘይቶች ላይ የሚገኘው ‹‹ ‹‹ሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ›› ከፍተኛ መሆኑን እና በሰው ልጅ ከሚያስፈልገው መጠን በላይ መሆኑ የጤና ችግር እንደሚያስከትል መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

የጥናቱ ውጤት እንዳሳየውም የኮሌስትሮል መጠን እንዲጨምር አድርጓል፡፡ ይህ ደግሞ ለልብ እና ለሌሎች ተዛማጅ የማይተላለፉ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ ተነግሯል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ባደረገው ጥናት የፓልም ዘይት ከ50 እስከ 80 በመቶ ‹‹ሳቹሬትድ ፋቲ አሲድ›› እንዳለው መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

የፓልም ዘይት ደግሞ በዝቅተኛ እና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል በስፋት የሚጠቀመው ነው፡፡ የጥናት ውጤቱም ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደተላከ ተገልጧል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እና ለንግድ ሚኒስቴር ጥቆማውን እንዳቀረበ ታውቋል፡፡

ህብረተሰቡም የፓልም ዘይትን መጠቀም እንደሌለበት እና አቅም በፈቀደ መጠን ጥራት ያላቸውን ዘይቶች እንዲጠቀም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስጠንቅቋል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE