ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

Image may contain: sky, tree, grass, cloud, outdoor and natureበአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በዛሬው ዕለት በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።

አደጋውን ተከትሎ በአካባቢው በተደረገ ቁፋሮ አንድ የ70 ዓመት አዛውንት በህይወት ማውጣት ቢቻልም አለርት ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

አደጋው የደረሰው ቆሻሻ ከተጠራቀመበት አካባቢ ላይ ከተሰሩ የፕላስቲክ ቤቶች እና መንገድ ዳር በመሆኑ እስካሁን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።

አሁን ላይም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቆሻሻው በተደረመሰበት አካባቢ የሰው ህይወት ለማዳን በኤክስካቫተር የታገዘ ቁፋሮ እያካሄዱ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከሁለት ዓመት በፊት በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

FBC

Image may contain: sky, outdoor and nature


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE