«ከዩኒቨርስቲው ወጥተን ወደ መጣንበት መመለስ ነው የምንፈልገው” – በትግራይ ክልል የተመደቡ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች

በመቀሌ ከተማ የሚገኙ የአክሱም የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ እዛው ግቢ ውስጥ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ። ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው የፀጥታና ድህንነት ስጋት መኖሩን በመጥቀስ የፌዴራል መንግስት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡ ለዶቼ ቬለ «DW» አስተያየታቸውን የሰጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ ስለሚያሰጋቸው «ከዩኒቨርስቲው ወጥተን ወደ መጣንበት መመለስ ነው” የምንፈልገው ብለዋል፡፡ « ዛሬ ምሳ ሰዓት አካባቢ ራሱ ግጭት ሊከሰት ነበር። ያለውን ሁኔታ ለመግለፅ ይከብደኛል። ይህ ነገር ተደምሮ ተማሪውን ወደ ቁጣና ተስፋ መቁረጥ አስገብቶታል» የአክሱም ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር በበኩሉ በአሁኑ ወቅት በዩኒቨርሲቲው በቂ የፀጥታ ኃይል መኖሩን በመጥቀስ ለተማሪዎች ድህንነት ስጋት የሆነ ችግር የለም ይላል፡፡ የተቋረጠው ትምህርትና ፈተናም ከመጪው ሳምንት ጀምሮ እንደሚቀጥል ተቋሙ ገልጿል፡፡ በአክሱም ዩንቨርስቲ ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በተፈጠረ ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲጠፋ ሰባት ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ዩንቨርስቲው አስታውቆ ነበር።

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE