አንድ ወደፊት ኹለት ወደኋላ! ፓትርያርኩ፥ የመሪ ዕቅድ ዐቢይ ኮሚቴን አግጃለኹ፤ ሲሉ ጉባኤው፥ እንደገና ይዋቀር፤ አለ! እንዳንለወጥ ተረግመናል!?

ደኅና ተቋቁሞ ሥራ የጀመረው የመሪ ዕቅድ ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ ፈርሶ፣ በቀጣዩ ቋሚ ሲኖዶስ ክትትል እንደገና እንዲዋቀር ምልአተ ጉባኤው ዛሬ ከቀትር በፊት ወሰነ፤ በስብሰባው መራዘም የተሰላቸ የሚመስለው ምልአተ ጉባኤ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ትግበራውን እንዲያስፈጽም ማዘዙን ማስታወስና ፓትርያርኩም ማገድ እንዳይችሉ መከላከል ተስኖታል! ፓትርያርኩ፣ የቀድሞው ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ሠራተኛ እንዳይቀጥሩ ያስተላለፉት ሕገ ወጥ እገዳ፣ የሞያተኞች ቅጥር ማስታወቂያ የወጣበትን የለውጥ ግስጋሤ ለማስቆም እንደነበር አምነዋል፤ …

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE