ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብጽን ለ16ኛ ጊዜ ለመጎብኘት ካይሮ ገብተዋል

– እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1993 ጀምሮም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ግብፅን ከ16 ጊዜ በላይ መጎብኘታቸው ነው ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የግብፅ ከፍተኛ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በግብፅ በሚኖራቸው የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝትም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ ኤል ሲሲ ጋር በሁለትዮሽና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።እንዲሁም ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር በአፍሪካ እየተከናወኑ ባሉ አሁናዊ ለውጦች ዙሪያ የሚወያዩ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግብፅን ሲጎበኙ ይህ ለአራተኛ ጊዜያቸው ነው ተብሏል።ኤርትራ ነጻነቷን ካወጀችበት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1993 ጀምሮም ፕሬዚዳንቱ ግብፅን ከ16 ጊዜ በላይ መጎብኘታቸው ነው የተገለፀው።

FBC


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE