ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ኾነው በምልአተ ጉባኤ ተመረጡ

በሕጉ መሠረት፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የብፁዕ ዋና ጸሐፊውን መሠየም በደብዳቤ ይገልጹላቸዋል፤ የተመረጡትን ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በፊርማቸው ይሾሟቸዋል፤ ብፁዕ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዮሴፍ፣ የሕፃናት እና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅትንም በቦርድ ሰብሳቢነት ይመራሉ፤ ተሰናባቾቹ፥ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ በምልአተ ጉባኤው አባላት ሽልማትና ከፍተኛ ምስጋና ተሸኙ! ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ሀገረ ስብከታቸውን …