የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በእንጦጦ ተራራ ችግኝ ተከሉ

ከ30 ያላነሱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ዛሬ ዓርብ፣ ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ረፋድ፣ በእንጦጦ ተራራ የደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ችግኞችን የተከሉ ሲኾን፣ የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን፣ የተከላ መርሐ ግብሩን አስተባብሯል፡፡ ዝግባ፣ ወይራ፣ ዘንባባን ጨምሮ ከ150 በላይ የአገር በቀል ዐጸዶች ችግኞች ተተክለዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የተናገሩት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘካናዳ፣ ዐጸዶችን መትከልና …