ዘጠኝ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድነት ብሄራዊ ግንባር የሚል ፖርቲ በመመስረት መወሃዳቸውን አስታወቁ፡፡

ዘጠኝ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድነት ብሄራዊ ግንባር የሚል ፖርቲ በመመስረት መወሃዳቸውን አስታወቁ፡፡

የተዋሃዱት ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ኮንግረስ፣ የኢትዮጲያ ህብር – ህዝብ ብሄራዊ ንቅናቄ፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ህብረት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኮንግረስ፣ የጋንቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የጋንቤላ ህዝብ ፍትህ፣ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ፣ ሼኮና አካባቢው ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና የአርጎባ ብሄረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው፡፡

ግንባሩ ሰላማዊ የትግል ስልትን በመቀየስ አዲስ እና የተሻለ ሊያሰራ የሚችል ጠንካራ የትግል ትብብር መስርቶ በህብረት መስራትን ዓላማ አድርጎ የተዋሀደ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይሄንን ግንባር ለመምራት ዋናና ምክትል አስተባባሪዎች፣ፀሀፊና ሁለት አባላት በድምሩ አምስት አባላት ያሉት ጊዜያዊ ኮሚቴ ተሰይሟል፡፡

ግንባሩን የመሰረቱ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች የጋራ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም የጋራ የአቋም መግለጫም አውጥተዋል፡፡

በቀጣይም ከግንባሩ ጋር ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ የሆነ አላማና ፕሮግራም ያለው ማንኛውም ፓርቲ ተቀላቅሎ በጋራ እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡