አባቶች ወደ ባለ ሥልጣናት ይሄዱ ነበር እንጂ መሪዎች ወደ አባቶች መምጣት ቀርቶ ነበር – ቅዱስ ፓትርያርኩ

ጠሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በጠቅላይ ቤተ ክህንት የቅዱስ ሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ በመገኘት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ያላቸውን መልካም ምኞት ገለጡ።

Image may contain: 1 person, sitting and indoor

ቅዱስ ፓትርያርኩ የጠሚ/ሩ መምጣት የነበረውን ታሪክ የቀየረ ነው ብለዋል። አባቶች ወደ ባለ ሥልጣናት ይሄዱ ነበር እንጂ መሪዎች ወደ አባቶች መምጣት ቀርቶ ነበር። ለቅዱስ ሲኖዶስ አንድነትና ከ42 ዓመት በኋላ ለተመለሱት የ4 ኪሎ ሕንፃዎች ጉባኤው ምስጋና አቅርቧል።
ክቡር ጠሚሩ ለሲኖዶሱ ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት አምስት ነጥቦችን ለጉባኤው አደራ ብለዋል።

1. ቤተ ክህነት ጠንካራ፣ ከሙስና የጸዳ፣ ግልጽነት ያለው ተቋም እንዲሆን ብትሠሩ። ካህናትና ምእመኛናን ፍትሕ ፍለጋ በየ መንግሥት ተቋማቱ መሄድ አልነበረባቸውም።
2.በየአካባቢው ከሚገኙ የመስተዳድር አካላት ጋር በመሆን ሕዝቡን ስለ ሰላም፣ ፍቅርና ዕርቅ ብታስተምሩ፤ ብትሠሩ
3.ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር በመሆን ት/ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን፣ የርዳታ ተቋማትን ፣ የአካል ጉጉዳተኞች መርጃዎችን ብታቋቁሙ
4. ሕዝቡ ለበዓል ከአንዱ ቦታ ወደሌላው ለመሳለም ይሄዳልና ሕዝቡን ለማቀራረብ ፣ ለማገናኘትና አንድ ለማድረግ ብንጠቀምበት
5. በረመዳን ጾም የመጨረሸዎቹ ቀናት ሕዝበ ክርስቲያኑ የተለመደዉን በጎ ተግባር መስጊዶችንና አካባቢውን በማጽዳት አንድነታችንን ብናሳይ፤
6. በክረምት በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ለመትከል አስበናልና አባቶች ሕዝቡን ብታስተባብሩ፡

PMO Ethiopia

Image may contain: one or more people, people sitting and indoor