በአዲስ አበባ የራቁት ጭፈራ ቤቶች መስፋፋታቸው አሳሳቢ ሆኗል ተባለ

በአዲስ አበባ የራቁት ጭፈራ ቤቶች መስፋፋታቸው አሳስቦኛል”- የአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ቦሌ አካባቢ የራቁት ጭፈራ ቤቶች መስፋፋታቸው እንዳሳሰበው የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ከመጤ ባህል ጋር ተያይዞ የራቁት ጭፈራ ቤቶች መስፋፋታቸው ስለማይፈለግ በተለይ ቦሌ አካባቢ የሚገኙ በአፋጣኝ እንዲዘጉ ተደርገዋል፡፡

የራቁት ጭፈራ ቤቶች ያሉበትን በመጠቆም እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ እንደሚቻል ነው ቢሮው ያስታወቀው።

በተጨማሪ ቢሮው ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በድምጽ ብክለት እና በመጤ ባህል ህብረተሰቡን የጎዱ 231 የንግድ ድርጅቶች፣ ጭፈራ ቤቶች እና ጫት ማስቃሚያ እንዲሁም ሺሻ ቤቶችን ዘግቷል።

በተለይ በኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚገኙ ጭፈራ ቤቶች እየተዘጉ ይገኛል።

(ኢ.ፕ.ድ)