አሥራት ቲቪ ልደታ ፍርድ ቤት ተገኝቶ ድምፃቸውን ለማሰማት ሲጥር እንዳይቀርፅ በፖሊስ ክልከላ ተደርጎበታል።
የጉራጌ ሕዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት ቀናኢ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው። አኩራፊውን ሁሉ የሚያባብለው የኢትዮጵያ ሚዲያና ፖለቲከኛ የጉራጌን ሕዝብ ልክ እንደ አማራው “ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ” እያለ እንዲዘምር እንጅ ጩኸቱ እንዲሰማ አይፈልጉም። ድምፅም አይሆኑለትም። ከአማራው ቀጥሎ ለበርካታ ጊዜ ድምፅ አልባ የሆነው የጉራጌ ሕዝብ ነው። የጉራጌ ሕዝብ ልክ እንደ አማራው ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል ሁሉንም መከራ ይቀበል ተብሎ የተፈረደበት ሕዝብ ነው። ችግር ሲደርስበት የሚጮህለት ግን የለም።
ይህ ዝምታ መቀጠል የለበትም ያሉ የጉራጌ ተወላጆች ሰሞኑን የሚዲያዎችን በር አንኳኩተዋል። ነገር ግን ቀና ምላሽ የሰጣቸው አላገኙም። በትናንትናው ሰልፋቸው የተገኘው አስራት ብቻ ነው። ጉራጌ ስለ ኢትዮጵያ እንዲዘምር ሲፈለግ፣ የስራ ባሕሉን ለመግለፅ በርካታ ሚዲያ ይገኙ ነበር። ከጉራጌ ሕዝብ ለመጋራት ሲባል እንጅ የጉራጌን ሕዝብ መከራ ለመጋራት ብቅ የሚል የለም። ትናንትም አይተነዋል።
አሥራት ቲቪ ልደታ ፍርድ ቤት ተገኝቶ ድምፃቸውን ለማሰማት ሲጥር እንዳይቀርፅ በፖሊስ ክልከላ ተደርጎበታል። ያም ሆኖ የቻለውን ለማስተላለፍ ጥሯል!
የጉራጌን ሕዝብ የምንፈልገው የስራ ባሕሉን ለመቅሰም፣ ስለ ኢትዮጵያ እንዲዘምር ብቻ አይደለም። መከራውን መጋራት፣ ጩኸቱን ማሰማትም ያስፈልጋል።