ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተከሰተ ግጭት የብሔር መልክ ይዞ ጉዳት ደረሰ

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተከሰተ ግጭት የብሔር መልክ ይዞ ቢያንስ ሁለት ድብደባ የደረሰባቸው ተማሪዎች ሐኪም ቤት መግባታቸውን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ እና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ት መቅደስ ካሣሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናገሩ።የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አንዳንድ ተማሪዎች ከትናንት ጀምሮ ወደ ክልላችን እንመለሳለን ማለታቸውን ኾኖም ዩኒቨርሲቲው እንዳይወጡ እንደከለከላቸው ነዋሪዎች ገልጠዋል። ዩኒቨርሲቲው «ችግሮችን እንፈታለን፤ እንወያይና ያሉትን ነገሮች እንነጋገር» በሚል ከተማሪዎቹ ጋር ውይይት እያካሄደ መኾኑ ተገልጧል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ እና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ት መቅደስ ካሣሁን ተናገሩ።

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE