ኤርትራ ማህበራዊ ሚዲያን ዘጋች

ኤርትራ ማህበራዊ ሚዲያን ዘጋች

ኤርትራ ውስጥ የማህበራዊ ሚዲያ አገልገሎት መታገዱን ተከትሎ ህብረተሰቡ በቪፒኤን አማካይነት መልዕክት እየተለዋወጠ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።

ለማህበራዊ ሚዲያው መዘጋት ግልፅ ምክንያት ስለመኖሩ አልታወቀም።

ሆኖም ህዝቡ በፈረንጆቹ በመጪው ግንቦት 24 ቀን የሚከበረውን የነጻነት ቀን የሚያስተጓጉል ተቃውሞ እንዳይቀሰቅስ ለመከላከል ሊሆን እንደሚችል ዘገባው ያሳያል።

በኢንተርኔት የዓለም ደረጃዎች መሰረት ኤርትራ ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልገሎት ካላቸው ሀገራት ተጠቃሽ ናት።

በ2018 በተደረገ ዳሰሳ ከአጠቃላይ ህዝቧ ውስጥ የኢንተርኔት አገልገሎት የሚጠቀሙት 71 ሺህ ወይም ከአጠቃላዩ 1.3 በመቶ ብቻ መሆናቸው ተነግሯል።

ኤርትራ ውስጥ የግል ሚዲያ እንደሌለ የገለጸው ቢቢሲ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትም የለም ብሏል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE