ፖሊስ ወንጀልን በተደራጀ መልኩ ሲፈፅሙ የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ

ፖሊስ በአዲስ አበባ ቅዳሜና እሁድ ባካሄደው ዘመቻ ወንጀልን በተደራጀ መልኩ ሲፈፅሙ የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ

Image may contain: one or more people, people walking and outdoor

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቅዳሜ እና እሁድ ባካሄደው ኦፕሬሽን በመዲናዋ የተለያዩ ወንጀሎችን በተደራጀ መልኩ ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን እና ለወንጀል ተግባር ሲውሉ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ፖሊስ በልደታ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ ክፍለ ከተማዎች ባካሄደው ጥናት ላይ በተመሰረተ ዘመቻ እና ድንገተኛ ፍተሻ ሰነድ ሳይኖራቸው እና ህጋዊነታቸው ያልተረጋገጡ 260 ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

በህገ ወጥ ተግባር ላይም ማለትም በቅሚያ፣ በዝርፊያ፣ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና መድሃኒት ዝወውር ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Image may contain: one or more people, car and outdoor

በተጨማሪም ከአደገኛ እፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ትልልቅ ሆቴሎች የሚያርፍ የውጭ ሀገራት ዜጎችን በደላላ እና በሆቴል ሰራተኞች በኩል በማግባባት ሺሻ እና ባእድ ነገር ተቀላቅሎ ወደ ሚጨስባቸው ስፍራዎች በመውሰድ የወንጀል ድርጊት እንዲፈፀምባቸው ያደረጉ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

በቅንጅት የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ከ250 ሺህ ብር በላይ ትልልቅ ህንፃዎችን በመከራየት የወንጀል ድርጊት ሲፈፅሙ እንደነበርም አመልክተዋል።

Image may contain: table and outdoor

በሶስት ክፍለ ከተሞች በተደረጉ ዘመቻዎች ከ2 ሺህ 500 በላይ የሺሻ ማጨሻና እና መገልገያዎች ከዋና ዋና የድርጊቱ ፈፃሚዎች ጋር ተይዘዋል።

ግማሽ ኪሎ የሚደርስ አደገኛ እፅም በዘመቻው ተይዛል።

ፖሊስ ሺሻ ሲያጨሱ የተገኙ በርካታ ግለሰቦችን በመምከር እንደለቀቀም ነው የተመለከተው።

በመግለጫው ምን ያህል ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ አልተገለፀም።

Image may contain: plant


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE