ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በሚል ለመዋሀድ 5 ፓርቲዎች ተስማሙ

አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሢያዊ ፓርቲ በሚል ለመዋሀድ መሥማማታቸውን ገለጸዋል። .

5ቱ ፓርቲዎችም የኢትዮጵያ ትንሣኤ ዴሞክራሢያዊ ድርጅት/ ቱሣ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት /ሽግግር፤ ኢትዮጵያችን ህዝባዊ ንቅናቄ/ኢትዮጵያችን ፤ የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት /ኦህዴህ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት/ አረንጓዴ ኮከቦች ናቸው።

ፓርቲዎቹ የፊታችን ሀሙስ በይፋ ውህደታቸውን እንደሚፈጽሙም ተገልጿል።
ከቀናት በፊት 7 ፓርቲዎች ራሣቸውን አክስመው ኢዜማ የተሠኘ ፓርቲ መመሥረታቸው ይታወሣል።

አዲስ ቴቪ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE