የአርበኞች ግንቦት 7 መክሰምና የአዲሱ ፓርቲ ምስረታ – ያለፈው ሸክምና የወደፊት ሚና

የአርበኞች ግንቦት 7 መክሰምና የአዲሱ ፓርቲ ምስረታ፡፡ ያለፈው ሸክምና የወደፊት ሚና

Reyot News Magazine
አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች በየራሳቸው ህልውና ከነበራቸውና ፓርቲዎች ጋር በመዋሃድ አዲስ ፓርቲ መመስረቱን በመጨረሻ መግለጫው አስታውቋል፡፡ በርካታ ጥያቄዎችንም ጭሯል፡፡ ይህ አዲስ ፓርቲ ውጤት እንዲያመጣ መጠበቅና ተስፋ ማድረግ Benefit of doubt መስጠት የሚገባ መሆኑ ሳይዘነጋ፤

1 የአርበኞች ግንቦት 7 ከ10 አመታት በላይ ጉዞና በዚህ ሂደት የተፈጠሩት ውዝግቦች ጥላ ይህንን ፓርቲ በምን ልክ ተጽእኖ ሊያሳድርበት ይችላል?
በኤርትራ ትግል የማካሄድ ውሳኔውና ከሻቢያ ጋር የነበረውና አመራሮቹ አሁን ድረስ ያላቸው ግንኙነት፣
በአዲስአበባ ጉዳይ ላይ ያሳየው መጠን የለሽ ዝምታና ያወጣቸው ደጋፊዎቹን ቅር ያሰኙ መግለጫዎች፣
መሪው በአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት ዙርያ የሰጡት አስተያየት፣
በአሁን ወቅት ከኦዴፓና መሪዎቹ ጋር ድርጅቱ የነበረውና አመራሮቹ አሁን ድረስ እንዳላቸው የሚታወቅ ቅርበት፣
ከአማራ ብሄረተኞች ጋር የገባበት ግጭት ወዘተ እዚህ ላይ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

2 ፓርቲው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሜዳ የዜግነት ፖለቲካ የሚሹ በአስርት ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እውነተኛ ድምጽና ወኪል ሆኖ ሊወጣ ይችላል? የሚሉና ሌሎችም በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡
በነዚህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል፡፡

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE