የቀድሞው የደህንነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሀገር ውስጥ ይኑር አይኑር ማረጋገጥ አልችልም ! – ቢለኔ ስዩም

“አሁን ላይ (አቶ ጌታቸው) ሀገር ውስጥ ይኑር አይኑር ማረጋገጥ አልችልም!”

በኤልያስ መሰረት

ለዛሬው የጠ/ሚር ቢሮ ፕረስ ሰክረታሪ ጋዜጣዊ መግለጫ ወደ ግቢው እንደደረስን ውጪ በር ላይ ለግንቦት ማርያም የተዘጋጀ የስንዴ እና ሽንብራ ንፍሮ ተቀበለን። ወደ ውስጥ (ዋናው ቢሮ) ሲገባ ደሞ ሞቅ ተደርጎ የተከፈተ ሙዚቃ፣ የበአል ልብስ የለበሱ ሰዎች እንዲሁም በብዛት የተጎዘጎዘ ሳር ይታያል።

ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ ለውጭ ሀገር ሚድያ ጋዜጠኞች መግለጫውን የሰጠችው ቢለኔ ስዩም ነበረች። እኔም ሁለት ጥያቄዎችን ሰንዝሬ ነበር። ከእንግሊዘኛ የተተረጎመው ዝርዝር እነሆ:

ጥያቄ: የኢትዮ- ኤርትራ ድንበር መዘጋትን ተከትሎ መረጃ ለማግኘት ብንሞክርም አልተሳካልንም። ምክንያቱ ምንድን ነው? ድንበሩ የሚከፈትበት ቀን ይታወቃል?

ቢለኔ: በጉዳዩ ላይ የሚመክር ከኤርትራ የመጣ የልኡክ ቡድን ነበር፣ ከዚህም ወደ ኤርትራ ሄዶ የነበረ ልኡክ ነበር። የደረሱበትን ዝርዝር ስራቸውን ሲጨርሱ የሚያሳውቁን ይሆናል።

ጥያቄ: የቀድሞው የደህንነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ክስ እንደተመሰረተባቸው ሰምተናል። ወደ ህግ ለማቅረብ ምንድን ይደረጋል? እንደው ግለሰቡ ሀገር ውስጥስ አሉ ወይ?

መልስ: አሁን ላይ (አቶ ጌታቸው) ሀገር ውስጥ ይኑር አይኑር ማረጋገጥ አልችልም። ነገር ግን በአቃቤ ህግ እና በሌሎች የፀጥታ ተቋማት እሳቸውንም ይሁን ሌሎችን ወደ ህግ ለማቅረብ ጥረት ይደረጋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE