ከኤርትራ የተመለሱ የአዴሀን ታጋዮች መንግስት የገባልነን ቃል አላከበረም ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

ዛሬ ግንቦት 1/2011 ዓ.ም ባህርዳር ከተማ የአዴሃን ታጋዮች ሰልፍ አድርገዋል።

ታጋዮቹ ሰልፍ ለማድረግ የተነሳሱት ለአማራ ህዝብ መብት መከበርና በጉልበት የተዘረፍ የአማራ እርስቶችን ለማስመለስ ለ8 ዓመታት በበርሃ ታግለን፣ለውጥ መጣ ተብሎ ወደ አገርቤት ከገባን በኋላ ተጥለናል በማለት ነው።ታጋዮቹ “መንግስት የገባልነን ቃል አላከበረም” ሲሉ አዴፓን ከሰዋል።

“ለሰላም የተዘጉ በሮች በአመጽ ይከፈታሉ!! ሲሉም ለክልሉ መንግስት ማስጠንቀቂያ አዘል መፈክር አሰምተዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE